ይህን ያውቁ ኖሯል?
1. በኢፌዲሪ ህገ-መንግስት የተቀመጡ መብት እና ግዴታዎች
- ሁሉም ሰዎች ንጹህና ጤናማ በሆነ አካባቢ የመኖር መብት አላቸው (አንቀፅ 44)
- መንግስት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ንፁህና ጤናማ አካባቢ እንዲኖረው የመጣር ሃላፊነት አለበት (አንቀጽ 92)
- ማንኛውም የኢኮኖሚ ልማት እርምጃ የአካባቢውን ደህንነት የማያናጋ መሆን አለበት (አንቀጽ 92)
- መንግስትና ዜጎች አካባቢያቸውን የመንከባከብ ግዴታ አለባቸው (አንቀጽ 92)
2. የዛፍ መቁረጥ፣ ማዘዋወርና የደን ውጤቶች የይለፍ ፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ቁ/01/2014 ላይ የተቀመጡ መብት እና ክልከላዎች
ማንኛውም ህጋዊ ሰው፤ የመንግስተ ተቋም፤ግል አልሚ ወይም ባለይዞታን ጨምሮ በባለስልጣን መ/ቤቱ ወይም በክ/ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ተጠንቶ እና ተረጋግጦ ከሚሰጠው ፈቃድ ውጪ ዛፎች መቁረጥ አይችልም (አንቀጽ 26)
- ከመንግስት፣ ከተቋማት እና ከግል ይዞታዎች ያለ ፈቃድ ዛፎች የቆረጠ ፣ያመረተ፣ያከማቸ ማንኛውም ሰው የደን ውጤቱን ባለው የህግ አግባብ መወረሱ እንደተጠበቀ ሆኖ ከአንድ አመት በማያንስና ከአምስት አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እና ከአስር ሺህ እስከ ሃያ ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል (አንቀጽ 26)
- ያልተፈቀደ የደን ወጤት ያጓጓዘ ማንኛውም ሰው ከ6 ወር በማያንስና ከ1 አመት የማይበልጥ ቀላል አስራትና ከብር 5 እስከ 10 ሺ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል (አንቀጽ 27)
- ዝርያቸው በመጥፋት የሚገኙ የዛፍ ዓይነቶች በህገወጥ መንገድ ከመንግስት፣ከተቋማት፣ ከግል ይዞታ ላይ የቆረጠ፣ ያጓጓዘ፣ ያከማቸና ለሽያጭ ያቀረበ ከአምስት አመት በማይበልጥ ጽኑ አስራትና ከ15 ሺ ( አሰራ አምስት ሺ ብር) እስከ 20 ሺ (ሃያ ሺ ብር) በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል (አንቀጽ 27)
የኮንስትራክሽን ማዕድን የማምረት ፈቃድ የማይሰጥባቸው ቦታዎች
- ፈቃድ ሰጭው ባለሥልጣን በልዩ ሁነታ ወይም ስለቦታው የሚመለከተው ህጋዊ አካል /ባለቤት/ ካልፈቀደ በስተቀር
- ለመቃብርና ሃይማኖታዊ ጉዳዮች በተከለሉ ቦታዎች
- የቅድመ ታሪክ ቅሪቶች ባሉባቸው ወይም ብሔራዊ መታሰብያዎች በቆሙባቸው ስፍራዎች
- ለመሰረተ ልማት አውታሮች በተከለሉበት ቦታዎች
- ለተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ ወይም በብሔራዊ ፓርክ በተከለሉ ስፍራዎች
- ከከተሞች ወይም ከውሃ ማጠራቀምያዎች (ግድቦች) በ500 ሜትር ክልል ውሰጥ
- ከህጋዊ ይዞታ መንደሮች 50ሜትር ከኤሌክትሪክ ተሸካሚ 25ሜትር ክልል ውሰጥ ፈቃድ አይሰጥም
አስተዳደራዊ ቅጣት የሚያስከትሉ ጥፋቶች
- በኮንስትራክሽን ማዕድን ማምረት ፈቃድ ውል ላይ የተመለከቱትን ግዴታዎች አለማክበር
- ያለ ማዕድን ምርት ሽያጭ መቆጣጠርያ ደረሰኝ የሚሸጡ፣ የሚሰርዙ፣የሚደልዙ፣ በበራሪውና በቀሪው ደረሰኝ ላይ የተለያየ መረጃ የሚመዘግቡ እና መሰል ጥፋቶችን ለሚያከናውኑ፣
- በወቅቱ ፍቃዳቸውን የማያሳድሱ፣ ሮያሊቲ የማይከፍሉ
- የድንበር መለያ ምልክት የሆኑትን የወሰን ድንጋዮች ያጠፋ ወይም የነቀሉ
- ከቢሮው የሚሰጠው የማዕድን ምርት ሽያጭ መቆጣጠሪያ ደረሰኝ ቅጽ በተለያዩ ምክንያቶች ያጠፋ፣በራሪውንና ቀሪው ላይ ልዩነት ሲኖር እና ዋጋ ሳይጻፍ ሲቆርጡ
- ሕጋዊ የማዕድን ማምረት ፈቃድ እያላቸው ተከልሎ ከተሰጣቸው ቦታ አልፈው ለሚያመርቱ ወይም ያለፈቃድ በሕገወጥ መንገድ ማዕድናትን ለሚያመርቱ
- ለማንኛውም አሽከርካሪ የኮንስትራክሽን ማዕድናትን ከማምረቻ ቦታ ጭኖ በሚንቀሳቀስበት ወቅት የማዕድን ሽያጭ መቆጣጠሪያ ደረሰኝ የማይቆርጡ ከሆነ