`

የዜጎች የስምምነት ሰነድ |
Citizens Charter

በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በብቃትና ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመወጣትና ያስቀመጠውን ራዕይ፣ተልዕኮና ዕሴት ለማሳካት ያስችለው ዘንድ አዳዲስ አሰራሮችን በስራ ላይ በማዋል እና እንዲሁም በሃገር አቀፍ የተጀመረውን ሃገራዊ ለውጥ በማሳካት ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን ማስመዘገብ ተችሏል፡፡

ከዚህ አንፃር የምንሰጣቸውን አገልግሎቶች ተገልጋዩን በማሳተፍ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው የመልካም አስተዳደር ስርዓት በማስፈን በሴክተሩ ስር የሚገኙ ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎቶች ከስታንዳርዳቸው እንዲሁም የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት በመዘርጋት የተገልጋዩን ህብረተሰብ መብትና ግዴታዎች ያካተተ የዜጐች የሥምምነት ሰነድ ማዘጋጀትና ግልጽ ማድረግ በማስፈለጉ ይህ የዜጐች የስምምነት ሰነድ ዕቅድ ተዘጋጅቷል፡፡

የዜጎች ስምምነት ሰነድ ዓላማ

  1. በጽ/ቤታችን ደረጃ የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ፣ውጤታማ፣ ሁሉን አቀፍ ተደራሽ በማድግ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ፍትሃዊ የመልካም አስተዳደር ሥርዓትን ለመዘርጋትና በሃገር ደረጃ የተጀመረውን ፈጣን ለውጥ ውጤታማ ለማድረግ መስራት፡፡

የዜጐች የስምምነት ሰነድ አስፈላጊነት

  1. ለተገልጋዩ ህብረተሰቡ የሚሰጡ አገልግሎቶችን የጥራት ደረጃ ለማስጠበቅ፣ የቅሬታ አቀባበልና አፈታት ሥርዓትን ለማሻሻል፣ ዜጐች የመገልገል መብታቸውን ለማረጋገጥ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራርን ለማስፈን የዜጐች የስምምነት ሰነድ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት

    የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት በዝርዝር ለማወቅ ከፈለጉ ይህን Duties and Responsibility ይጫኑ

የተገልጋዮች መብት

  1. ምንም ልዩነት ሳይደረግበት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የመሆን፣
  2. ማንኛውም ተገልጋይ በአገልግሎቱ አሰጣጥና በአገልግሎት ሰጪው ቡድን/ሠራተኛ ላይ ያለውን አስተያየትና ቅሬታ የማቅረብ፣
  3. በጽ/ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዝርዝር የማወቅና የመጠቀም፤
  4. ተገቢ የሆነ ድጋፍና እገዛ የማግኘት፤
  5. ቀልጣፋ አገልግሎት የማግኘት፤

የተገልጋዮች ግዴታዎች

  1. ሕጎችንና የአሰራር መመሪያዎችን መከተል
  2. ለሚፈልጉት አገልግሎት የተሟላና ትክክለኛ መረጃ የማቅረብ፣
  3. ተገልጋዬች አገልግሎት ለማግኘት ሲመጡ
    ተፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን የማሟላት