በቦሌ ክ/ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ዋና ዋና አገልግሎቶች
- 1. በአካባቢ ብክለት እና ተጽእኖ ግምገማ ቡድን የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
- ስለአካባቢ ብክለት፣ህጎችና የአፈፃፀም መመሪያዎች ለህብረተሰቡ ስልጠናና ግንዛቤ መስጠት
- ብክለት በሚያደርሱ ተቋማት ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ፣
- የብክለት መጠን በመለካት እርምጃ መውሰድ ፣
- የፕሮጀክቶችን የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ሰነዶችን በመገምገምና መቆጣጠር የማስተካከያ ሀሳብ መስጠት
- የአካባቢ አያያዝ ዕቅድ እና የአካባቢ ተፅእኖ ክዋኔ ሪፖርት መከታተል
- 2. በአየር ንብረት ለውጥ ቡድን የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
- ስለአየር ንብረት ለውጥ፣ ህጎችና የአፈፃፀም መመሪያዎች ለህብረተሰቡ ስልጠናና ግንዛቤ መስጠት፣
- ለአየር ንብረት ለውጥን በዘርፍ መ/ቤቶች በዕቅድ መካተቱን ማረጋገጥ ፣
- ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ተጋላጭ የህበረተስብ ክፍሎች ድጋፍና ክትትል ፣
- የኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን የዲዛይንና የፕሮሞሽን ስራ በመስራት ለተጠቃሚዎች ማስፋፋት፥
- 3. በየተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ቡድን አገልግሎት የሚሰጡ አገልግሎቶች
- ስለህጎችና የአፈፃፀም መመሪያዎች ለህብረተሰቡ ስልጠናና ግንዛቤ መስጠት፣
- በጥናትና ምርምር የተመሰረተ የብዝሃ ህይወትና ሥርዓተ ምህዳር ቁጥጥርና ክትትል ማድረግ፣
- በብዝሃ ሕይወትና ሥርዓተ ምህዳር ዙሪያ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠት፣
- የአረንጓዴ ቦታዎች ለታለመላቸው ዓላማ መዋላቸውን መከታተልና መቆጣጠር፣
- የደን ሃብት ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዲሰጥ ማድረግ ፣
- 4. በ ማዕድን ሀብት ፈቃድና አስተዳደር ቡድን የሚሰጡ አገልግሎቶች
- ስለማዕድን ሀብት ህጎችና የአፈፃፀም መመሪያዎች ለህብረተሰቡ ስልጠናና ግንዛቤ መስጠት፣
- ለአዲስ እና ነባር የኮንስትራክሽን ማዕድን ፈቃድ አስተያየት መስጠት ፣
- ነጭ ድንጋይ ማምረት ፈቃድ ፣ የወንዝ ዳር አሸዋ ማውጣት ፈቃድ ፣
- በማዕከልና በክ/ከተማ የተሰጡ ፈቃዶችን ማስተዳደር/መከታተል፣ መቆጣጠርና መረጃ ማደራጀት