የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ለማቋቋም እንደገና በወጣው አዋጁ ቁጥር 84/2016 መሰረት አደረጃጀቱ በከተማና በክፍለ ከተማ ብቻ እንዲሆን ተደርጎ ተደራጅቷል፡፡ በዚህም መሰረት በተሰጠዉ ስልጣንና ኃላፊነት የአካባቢ ብክለት ክትትልና ቁጥጥር ላይ በርካታ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ህብረተሰቡ የሚያነሳቸዉን የአካባቢ ብክለት ይወገድልኝ ጥያቄዎችን በሚፈለገዉ ልክ ምላሽ እንዳልተሰጠ እና የአካባቢ ብክለት ጉዳይ ትኩረት ሳይሰጠው በተጨባጭ ወደ ተግባር ሳይቀየር ቆይተዋል፡፡
ሆኖም አሁን በመሪዎች ደረጃ ልዩ ትኩረት በመስጠት የአካባቢ ብክለት አሳሳቢነት ሁሉም ተረድቶ መከላከል እና እያንዳንዱ ዜጋ የራሱን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ ስለሆነም የቦሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት በወረደለት አቅጣጫ መሰረት የክፍለ ከተማውን ነዋሪዎች በማስተባበር የተለያዩ የንቅናቄ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ በተጨማሪ "ብክለት ይብቃ ዉበት ይንቃ "በሚል መሪ ቃል ሰፊ የንቅናቄ ስራዎችንም ሰርተናል
አቶ አሜን ቅጣዉ , የቦሌ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ