በቦሌ ክፍለ ከተማ
የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት

በቦሌ ክፍለ ከተማ
የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት

በቦሌ ክፍለ ከተማ
የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት

የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ለማቋቋም እንደገና በወጣው አዋጁ ቁጥር 84/2016 መሰረት አደረጃጀቱ በከተማና በክፍለ ከተማ ብቻ እንዲሆን ተደርጎ ተደራጅቷል፡፡ በዚህም መሰረት በተሰጠዉ ስልጣንና ኃላፊነት የአካባቢ ብክለት ክትትልና ቁጥጥር ላይ በርካታ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ህብረተሰቡ የሚያነሳቸዉን የአካባቢ ብክለት ይወገድልኝ ጥያቄዎችን በሚፈለገዉ ልክ ምላሽ እንዳልተሰጠ እና የአካባቢ ብክለት ጉዳይ ትኩረት ሳይሰጠው በተጨባጭ ወደ ተግባር ሳይቀየር ቆይተዋል፡፡

ሆኖም አሁን በመሪዎች ደረጃ ልዩ ትኩረት በመስጠት የአካባቢ ብክለት አሳሳቢነት ሁሉም ተረድቶ መከላከል እና እያንዳንዱ ዜጋ የራሱን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ ስለሆነም የቦሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት በወረደለት አቅጣጫ መሰረት የክፍለ ከተማውን ነዋሪዎች በማስተባበር የተለያዩ የንቅናቄ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ በተጨማሪ "ብክለት ይብቃ ዉበት ይንቃ "በሚል መሪ ቃል ሰፊ የንቅናቄ ስራዎችንም ሰርተናል ... ተጨማሪ ያንብቡ

አቶ አሜን ቅጣዉ , የቦሌ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ
image description

በጽ/ቤቱ የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት

በቦሌ ክ/ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት:-

በዝርዝር ይመልከቱ

በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቦሌ ክ/ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

በተጨማሪም በጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ግንዛቤ በመፍጠር በዚህም ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂት ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሱቡ ከጽ/ቤቱ ጎን እንዲቆሙ እናሳስባለን፡፡

ጥያቄ ካልዎት እባክዎ ለመደወል አያመንቱ ወይም ይጎብኙን!!

+251983065481
+251912689710

አድራሻችን:-

የቦሌ አስተዳደር ህንጻ 5ኛ ወለል
የስራ ሰዓት ከሰኞ - አርብ ከጠዋቱ 2፡30 - ቀኑ 11፡30