image
image
image
image
image

በኢትዮጵያ እየተሰሩ ካሉ ስራዎች እንደ አዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት ልቤን የሚያሞቀው የለም፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሰኔ 1, 2017
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ "በኢትዮጵያ እየተሰሩ ካሉ ስራዎች እንደ አዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት ልቤን የሚያሞቀው የለም" ሲሉ ተናግረዋል። ብዙ ሰው አልቆ ስላላየው ባይረዳውም፤ የተሰራው የአፈር እና ውኃ ጥበቃ ስራ ትልቅ ነውም ብለዋል። ከዚህ በፊት እንጦጦን መንገድ እና መዝናኛ ሰርተን ወደ ፓርክ ቀይረነዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ነገር ግን በውስጡ ያለው ባሕር ዛፍ የአፈር መሸርሸርን ሊቋቋም ባለመቻሉ አሁን ላይ እርከን በስፋት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ስለ ትውልድ እያሰብን ለትውልድ የሚተላለፈውን አፈር ካልጠበቅን ጉዳቱ የከፋ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህም በሺህ ዓመታት የማንተካውን አፈር ለመጠበቅ ሲባል የሚሰራ እርከን መሆኑንም ነው የገለጹት። ውጤቱን ዛሬ ላይ ባናየውም ከ5 እና 10 ዓመታት በኋላ በሀገር በቀል ዛፎች የተዋበ፤ በእርከን የተደገፈ እና ውኃ የማይሸረሽረው ሥነምህዳር ማየታችን አይቀርምም ነው ያሉት። ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ እየተሰራ ያለው የወንዝ ዳርቻ ስራ ሰፊ መሆኑን ጠቁመው፤ በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት በአካባቢው ላይ የሚፈጠረውን ትልቅ ለውጥ እናያለን ብለዋል። ይህ ውጤት ከአካባቢ ጥበቃ አልፎ ጥቅሙ ለብዙዎች የሚተርፍ እንደሆነም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ያነሱት። በሰለሞን ከበደ #ebcdotstream #EBC #PM #AbiyAhmed #Ethiopia #AddisAbaba #የወንዝ_ዳርቻ_ልማት

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች