image
image
image
image
image

በሰላም ምንነት እና ሀገር ወዳድነት ዙሪያ ለቦሌ ክፍለ ከተማ ሴቶች ማኅበር አባላትና አመራሮች ሥልጠና ተሰጠ፡፡

ነሀሴ 22, 2017
ማኀበሩ ከቦሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ባዘጋጀውበዚህ ሥልጠና የሰላም ምንነት፣ አስፈላጊነት እና የሀገር ፍቅር ምንነትን በተመለከተ ገለጻ የተደረገ ሲሆን፣ ሰላም በማንኛውም መስክ ለሚከናወኑ ተግባራት ዋነኛ መሠረት እንደመሆኑ ሰላምን በማስፈን ረገድ የኀብረተሰቡ ግማሽ አካል የሆኑት ሴቶች የማይተካ ሚና እንዳላቸው በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡ ሴቶች ለሀገር ግንባታ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ በቀላሉ የማይለካ በመሆኑ በከፍተኛ የሀገር ፍቅር መንፈስ ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመመሥረት በሚደረገው ርብርብ ግንባር ቀደም ሆነው ድርሻቸውን እንዲወጡ በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም በተጨማሪ ተመልክቷል፡፡ የቦሌ ክፍለ ከተማ ሴቶች ማኅበር ሰብሳቢ ወ/ሮ መሠረት ሶርሳ በሥልጠናው ወቅት እንደተናገሩት ማኀበሩ የሴቶችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ተሳትፎ ለማሳደግ ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፣ የሴቶች ተሳትፎ በሰላም ግንባታ ላይ ጉልህ ቦታ እንዳለው አመልክተዋል፡፡ የሀገር ፍቅር በተግባር የሚገለጽ ሊሆን እንደሚገባ ያመለከቱት ሰብሳቢዋ፣ ሴቶች በዚህ መስክ በተለይም በሰላም ግንባታ፣ በመልካም አስተዳደር፣ በልማትና ሌሎችም መስኮች የዜግነት ድርሻቸውን በግንባር ቀደምትነት እየተወጡ እንደሚገኝ በመግለጽ ሥልጠናው የማኅበሩ አመራሮችና አባላት በሰላም ግንባታ መስክ በጠንካራ ሀገራዊ ፍቅር ሚናቸውን በበለጠ እንዲያጠናክሩ የሚያስችል እንደሆነ አክለው ተናግረዋል፡፡ ነሐሴ 22/2017

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች