image
image
image
image
image

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር “ጽዱ ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል የአካባቢ ጥበቃ ንቅናቄ አካሄደ፡፡

ሀምሌ 6, 2017
በንቅናቄው ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያን ንጹህና ጽዱ ለማድረግ እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃ ሥራን የማኀበረሰብ ባሕል እንዲሆን በርካታ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ መሆናቸውን አውስተው፣ የእነዚህ ተግባራት አካል በሆነው የ “ጽዱ ኢትዮጵያ” ንቅናቄ አዲስ አበባም የበኩሏን ሚና እየተወጣች እንደምትገኝ አመልክተዋል፡፡ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ “ጽዱ ኢትዮጵያ” ንቅናቄን በማስጀመር ላሳየው እንቅስቃሴ ዋና ሥራ አስኪያጁ ምስጋና አቅርበው፣ መላው የክፍለ ከተማው ማኅበረሰብም በዚህ እንቅስቃሴ በመሳተፍ ጽዱና ውብ አዲስ አበባን ለመፍጠር በሚደረገው ርብርብ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር እሸቱ ለማ በበኩላቸው ባለፉት ዓመታት ለአካባቢ ጥበቃ በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት አዲስ አበባ ለነዋሪዎችና ለጎብኚዎች ምቹ እንድትሆን እንዲሁም የአየር፣ የውሃ እና የአፈር ብክለትን ጨምሮ በአካባቢ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያደርሱ ችግሮችን ለመከላከል አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡ በክፍለ ከተማው የሚካሄደው የ “ጽዱ ኢትዮጵያ” ንቅናቄ እነዚህን ተግባራት ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ለኑሮ ምቹ አካባቢን ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸው፣ በንቅናቄው ኅብረተሰቡን በንቃት በማሳተፍ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት መሥራት እንደሚኖርባቸው አክለው አስገንዝበዋል፡፡ ሐምሌ 2/2017

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች